የመመሪያ መለያ: 983/2016
ቀን: ጥር 21፥ 2016 ዓ.ም.
Language: Amharic

ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የተፈራረሙትን የጠረፍ ንግድ ፕሮቶኮል ለማስፈጸም የወጣ መመሪያ ቁጥር 983/2016

ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን በሚዋሰኑባቸው የድንበር አካባቢዎች የሚገኙ የሁለቱ ሀገራት ሕዝቦች ከመሀል ሀገር በቀላሉ ሊያገኟቸው የማይችሏቸውን የፍጆታ እቃዎች በጠረፍ ንግድ አማካኝነት እንዲቀርቡላቸው ለማድረግ የሚያስችል የጠረፍ ንግድ ፕሮቶኮል እ.ኤ.አ. ፌብሯሪ 24 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ ላይ የተፈራረሙ በመሆኑ፤

ተፈራራሚ ሀገራቱ የጠረፍ ንግድ ማስፈጸሚያ መመሪያ በማውጣት ፕሮቶኮሉን መተግበር እንዳለባቸው በፕሮቶኮሉ አንቀጽ 4 ላይ የተመለከተ በመሆኑ፤

በድንበር አካባቢ ህጋዊ የጠረፍ ንግድ ስርዓትን መዘርጋት በአካባቢው የሚስተዋለውን የኮንትሮባንድ እና ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ለመቀነስ እና በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን ጎረቤት ሕዝቦች መካከል ያለውን ግንኙነት በማጠናከር በድንበር አካባቢ ሰላምና ፀጥታ ለማስፈን የሚረዳ መሆኑን በመገንዘብ፤

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 (እንደተሻሻለው) አንቀጽ 35 (2) እና 52(2) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር

Ministry of Trade and Regional Integration

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration