በማዕድን ዘርፍ ኢንቨስትመንት ለመሰማራት ለሚፈልጉ ፈቃድ ጠያቂዎች ፈቃድ አሰጣጥ ሁኔታዎችና የፈቃድ ዓይነቶች በማዕድን አዋጅ 52/1985 /እንደተሻሻለው/ በደንቡ 182/1986 የተደነገገ በመሆኑ፤
በአዋጅና በደንቡ የተደነገጉትን የፈቃድ ዓይነቶችና ፈቃዱን ለማግኘት የሚያስችሉ ቅደመ ሁኔታዎችን ግልፅነትና ተጠያቂነት ባለው መልክ ለማስፈጸም የሚቻልበትን አሠራር መቀየስ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
ማዕድን ሚኒስቴር በማዕድን አዋጅ ቁጥር 52/1985 አንቀጽ 46 ንዑስ አንቀጽ 3 አዋጁን ለማስፈጸም የሚያስችል መመሪያ ለማውጣት እንደሚችል በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡