በማዕድን ሥራ ባለፈቃድ ሊያዝ የሚችለዉ የፈቃድ ክልል ሥፋት ጣሪያ እንደ ማዕድኑ ተፈጥሮና አቀማመጥ እንዲሁም በአዋጪነት ጥናት ተረጋግጦ በተገኘው ክምችት መጠን መሠረት በማድረግ መወሰን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የሕግና የአሠራር ክፍተቶችን በመድፈንና ለማዕድን ሥራዎች ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ዓለም አቀፍና ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ባለሀብቶች በዘርፉ እንዲሠማሩ ማመቻቸት እንዳሁም በቂ አቅም እና ዝግጅት ሳይኖራቸው በዘርፉ የሚሠማሩ ባለፈቃዶች የማዕድን ቦታን ያለአግባብ ይዘው እንዳይቀመጡ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የማዕድንና የነዳጅ ሚኒስቴር በማዕድን ሥራዎች አዋጅ ቁጥር 678/2002 (በአዋጅ ቁጥር 816/2006 እንደተሸሻለው) አንቀጽ 82 ንዑስ አንቀጽ (2) እንዲሁም በማዕድን ሥራዎች የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 423/2010 አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀጽ (1) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡