የመመሪያ መለያ: 47/2013
ቀን: መጋቢት 22፥ 2012 ዓ.ም.
Language: Amharic

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሸከርካሪ ጎማ የመቆለፍ አሠራርን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 47/2013

በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ላይ እያታየ ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ እና አደጋዎች ከሚያስከትሉ የተለያዩ ምክንያቶች መካከል ህገ-ወጥ በሆነ መልኩ መንገድ ላይ ያለአግባብ ተሸከርካሪን ማቆም፣ ማሽከርከር በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ተሽከርካሪን ማሽከርከሪ እና ደህንነቱ ያልተጠበቀ ተሽከርካሪን ማሽከርከር የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 208/2003 እና በተሻሻለው ደንብ ቁጥር 395/2009 ላይ የተዘረዘሩ የመንገድ ትራፊክ ጥፋቶች ተፈፅመው ሲገኙ ሊወሰዱ የሚገባቸውን እርምጃዎች በተመለከተ ዝርዝር የማስፈፀሚያ ስልቶች ባለመዘርጋታቸው በተለይም የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ባልያዙ፣ በቦታው ባልተገኙም ሆነ በሌሎች ምክንያቶች አሽከርካሪዎች ላይ ሊወሰድ የሚገባው እርምጃ ግልፅ ባለመሆኑ የተሸከርካሪውን ሰሌዳ በመፍታት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላትን እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 64/2011 አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 11 የትራፊክ ደንቦች መከበራቸውን ቁጥጥር እንዲያደርግ አግባብ ባለው ሕግ ደንብ ተላላፊዎችን ላይ እርምጃ እንዲወስድና የማስፈፀሚያ ስልቶችን በመዘርጋት ተግባራዊነታቸውን እንዲያረጋግጥ ሥልጣን የተሰጠው በመሆኑ፣

የተሽከርካሪ ጎማ የሚቆለፍበት አግባብ፣ የተሽከርካሪ ጎማ ሲቆለፍ ሊወሰድ የሚገባውን ጥንቃቄ እና የተቆለፈው የተሽከርካሪ ጎማ ሊከፈት የሚችልበት ሥርዓት እና ሌሎች ጉዳዮችን መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ፣

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስፈፃሚ አካላትን እንደገና ለማደራጀትና ሥልጣንና ተግባራቸውን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 64/2011 አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ 3(ሠ) መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአዲስ አበባ ትራፊክ አስተዳደር ባለስልጣን

የአዲስ አበባ ትራፊክ አስተዳደር ባለስልጣን

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration