የመመሪያ መለያ: 276/2013
ቀን: መጋቢት 1፥ 1992 ዓ.ም.
Language: Amharic

የኢታኖል ቤንዚን ድብልቅ ነዳጅ ጥቅም ላይ ለማዋል የወጣ መመሪያ ቁጥር 276/2013

ከከርሰ ምድር የሚወጣው ነዳጅ ዘይት አላቂ ከመሆኑም በላይ በአብዛኛው ለትራንስፖርትና ኢንዱስትሪ አገልግሎት ሲውል የአካባቢ ብክለት የሚያስከትል በመሆኑ የነዳጅ ዘይት ሀብት ያላቸውና የበለፀጉ ሀገሮች ለታዳሽ ኢነርጂ ምንጮች ልማትና አጠቃቀም ከፍተኛ ትኩረት እየሰጡ ናቸው፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያም በግንቦት 1986 ዓ.ም. ዓ.ም. ባወጣችው የኢነርጂ ፖሊሲ ላይ ለትራንስፖርት አገልግሎት የሚውለው የነዳጅ ዘይት በከፊልም ቢሆን ለመተካት የሚያስችል የሀገር ውስጥ ምርት ጥቅም ላይ እንዲውል መንግሥት አስፈላጊውን ትኩረት እንደሚሰጥ ተመልክቷል። የአካባቢ ጥበቃና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፖሊሲዎችም ይህንኑ የትኩረት አቅጣጫ በበለጠ የሚያጠናክሩ ናቸው፡፡

በተለያዩ ሀገሮች ጥቅም ላይ ከዋሉት ታዳሽ የኢነርጂ ምንጮች መካከል ሞላሰስ ከሚባለው የስኳር ተረፈ ምርት _ ወይም ከተብላላ ስታርች የሚመረተው ኢታኖል የተሰኘው የአልኮል ዓይነት አንዱ ሲሆን በሀገራችንም የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ይህን ኢታኖል ማምረት ጀምሯል፡፡

በሀገር ውስጥ የተመረተውን ኢታኖል ከቤንዚን ጋር ደባልቆ ለገበያ ማቅረብ፡-

  • የውጭ ምንዛሪ ከማዳን፣ የአካባቢ ብክለት ከመቀነስ፣
  • የሀገር ውስጥ ተረፈ-ምርት ጥቅም ላይ ከማዋል፣
  • የነዳጅ ይዘትን (ኦክቴን ቁጥር) ከማሻሻልና ከተሽከርካሪዎች የሞተር ደኅንነት አኳያ ጠቀሜታ ስላለው ኢታኖል ከቤንዚን ጋር ተደባልቆ ጥቅም ላይ የሚውልበትን ስልት መቀየስ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበታል፡፡

በመሆኑም ይህን መመሪያ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል::

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስቴር

Ministry of Mines and Petroleum

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration