ባለስልጣኑ ለከተማው ነዋሪ የሚያቀርበውን ንጹህ የመጠጥ ውሃ ጥራትና መጠን በማሳደግ ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ስርጭቱን ለማስፋት እና ለደንበኞች የሚሰጠውን አገልግሎት ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነ የሚገኝ በመሆኑ፡፡
ይህም ዓላማ ግቡን ይመታ ዘንድ በስርጭት እና በአጠቃቀም ካላግባብ የሚባክነውን የውሃ መጠን መቀነሱ የውሃ ስርጭት የአቅርቦቱን መጠን ለመጨመር የሚረዳ በመሆኑና ደንበኞች በተለይም ትላልቅ የውሃ ተጠቃሚ ደንበኞች ውስን የሆነውን የውሃ ሀብት በአግባቡ የማይጠቀሙ በመሆኑና በዚህም የውሃ እጥረት እየገጠመ መሆኑ ደንበኞች ውሃ የማያበክኑ እና ውሃ ቆጣቢ እቃዎችን እንዲጠቀሙ ማድረጉ በአጠቃቀም ወቅት አላግባብ የሚባክነውን ውሃ መጠን ለመቀነስና የውሃ ስርጭቱን ፍትሃዊ እና ተደራሽ ለማድረግ የሚረዳ በመሆኑ፡፡
በአጠቃቀም ምክንያት አላግባብ የሚባክነውን ውሃ ለመቀነስ ደምበኞች የውሃ ቆጣቢ እና ውሃን ከብክነት የሚከላከሉ እቃዎችን እንዲጠቀሙ ለማድረግ የሚረዳ የአሠራር ሥርዓት ለመዘርጋት በማስፈለጉ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላት እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 35/2004 አንቀጽ 53 ንዑስ አንቀጽ 2 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡