የመመሪያ መለያ: 725/2013
ቀን: የካቲት 12፥ 2013 ዓ.ም.
Language: Amharic

የልማት ኃዩሎች እውቅና መስጫ መመሪያ ቁጥር 725/2013

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የሀገራችንን ራዕይ እውን ከማድረግ አንፃር የሚጫወተው ሚና ጉልህ እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን በተለይም ደግሞ አሁን በያዝነው የልማት ምዕራፍ ከተሞችን የኢንዱስትሪ መዳረሻ እንዲሆነ ከማድረግ አንፃር ከፍተኛ ተልዕኮ ተሰጥቶታል፡፡ የተልዕኮ ስኬቱ የልማት ኃይሎችን የጋራ እንቅስቃሴና ርብርብ የሚጠይቅ ሲሆን ከሁሉ በላይ ደግሞ የሰፊው የከተማ ነዋሪ ንቅናቄ ስምረት እንደሆነ እሙን ነው፡፡ ይህንን ንቅናቄ ለመፍጠርና ተልዕኮውን ለማሳካት በርካታ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ያሉ ሲሆን ከእነዚህ መካካል አንዱ በየዓመቱ የሚከበረው የኢትዮጵያ ከተሞች ሳምንት ነው፡፡

በዚሁ መሠረት በየዓመቱ በሚከበረው የኢትዮጵያ ከተሞች ሳምንት ላይ ከሚከናወኑት ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል አንዱ ሚኒስትሩ ለሚመራቸው ዘርፎች እድገት ጉልህ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የልማት ኃይሎች እውቅና መስጠት ነው፡፡ ከዚህ አንፃር የልማት ኃይሎች አስተዋፅኦ በየደረጃው በመለየትና በመገምግም ምርጥ ተሞክሮን ለመቀመርና ለማስፋት ብሎም በርካታ ሞዴሎች እንዲወጡ ለማጠናከር የሚያስችል ግልፅና ፍትሃዊ የአሠራር ስርዓት መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

በመሆኑም የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ዘርፉን ከመምራት አንፃር በተሠጠው ሥልጣን መሠረት ይህን የልማት ኃይሎች እውቅና መስጫ መመሪያ አውጥቷል።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን

Ministry of Urban and Infrastructure

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration