ወደ አገር የሚገቡ ሁሉንም መንገደኞች እና ዕቃዎችን መፈተሽ ከአገልግሎት አሰጣጥ፣ ከሃብት አጠቃቀም አንፃርና በአገር ገጽታ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚፈጥር ሆኖ በመገኘቱ፣
የሥጋት ሥራ አመራር መርህን በተከተለ መልኩ ከፍተኛ የሥጋት ደረጃዎችን በመለየትና የተመረጡ ስጋቶችን መሠረት ያደረገ ቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥና ውጤታማ የቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት ተገቢ በመሆኑ፣
በዚህም መሠረት በጥናት ላይ የተመሠረተ የመንገደኞችና የዕቃዎች ባህሪ የስጋት ደረጃ በመለየት የሥጋት ሥራ አመራርን ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣
የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 112(2) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡