የመመሪያ መለያ: 11/2012
ቀን: ነሐሴ 4፥ 2012 ዓ.ም.
Language: Amharic

የደንበኞች ፋይል አያያዝና አጠቃቀም መመሪያ ቁጥር 12/2012

የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣንና ተግባር ኃላፊነቱን በአግባቡ ለመወጣት በየጊዜው እያደገ የመጣውን የደንበኛውን የንፁህ መጠጥ ውኃ ፍላጎት ለማርካትና የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓቱን በማሻሻል ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ከሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ሥራዎች መካከል ዋንኞቹ የደንበኞች የውሃና የፍሳሽ መስመር ቅጥያ ሥራዎች ሲሆኑ በእነዚህ ሥራዎች ደንበኛው አገልግሎት ለማግኘት ከባለሥልጣኑ ጋር የሚዋዋለው ውል እና ከዚሁ ጋር ተያያዥ የሆኑ ሠነዶች የሚቀመጡበት የውል ማህደሮች በጥንቃቄ በተገቢው ቦታ መቀመጣቸው ለባለስልጣኑ የስራ አሠራርም ሆነ ለደንበኞች ቀልጣፋ እና ተገቢውን ምላሽና ማስረጃ ለመስጠት እንደሚረዳ በመታመኑ

አዲስ ቅጥያ፣ ማዛወሪያ፣ ማሻሻያና የፍሳሽ መስመር ቅጥያ እና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎች በጥንቃቄ በውል መዝገብ ቤት በየውል ቁጥራቸው ቅደም ተከተል ፋይል ተደርገው በተፈለጉ ጊዜ በቀላሉ ለማውጣትና ለባለስልጣኑም ሆነ ለደንበኛው ትክክለኛ የመረጃ ምንጭ በመሆን እንዲያገለግል ለማስቻል ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ሥርዓት ለመዘርጋት፣ የተሟላና ምቹ የሆነ የደንበኞች አገልግሎት መዝገብ ቤት አጠቃቀም ሥርዓት መኖር የጎላ ድርሻ ያለው በመሆኑ፡፡

የደንበኞችን መረጃ ደኅንነት ለመጠበቅ ከውል መዝገብ ቤት መረጃዎችን ለማውጣት የሚችል እነማን እንደሆኑ፣ ለምን ያህል ጊዜ በእጃቸው ማቆየት እንዳለባቸውና መቼ ለውል መዝገብ ቤት መመለስ እንዳላበቸው በዝርዝር የሚገልፅ ወጥነት ያለው የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት ያለበት መሆኑ ስለታመነ፤

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላት እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 35/2004 አንቀጽ 53 ንዑስ አንቀጽ 2 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

Addis Ababa Water and Sewerage Authority

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration