የኮሮና ወረርሽኝ በሀገራችን መከሰቱን ተከትሎ በባህል ዘርፍ በተለይም በእይታዊ፣ በትዕይንታዊ (ክውን) በስነ-ጽሁፋዊ ጥበባት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ በመፍጠር በሀገራችን ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ጥቅም ላይ ከፍተኛ ቀውስ በማስከተለ፤
በወረርሽኙ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የባህል ተቋማት አገልግሎት ጥንቃቄ በተመላበት መልኩ እንደገና በማስጀመር ያጋጠመውን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን መቅረፍ በማስፈለጉ፤
የባህል ተቋማት አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት ተገቢውን የደኅንነትና የጥንቃቄ እርምጃዎችን በመከተል አሰራራቸውን በተደራጀ መንገድ በማዘመን አገልግሎቱ ከስጋት በጸዳ አግባብ መምራት በማስፈለጉ፤ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር 1097/2011 አንቀጽ 30 ንዑስ ቁጥር 2 የባህል ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ደኅንነትን በማስጠበቅ ለማስፋፋት በማሰብ ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡