ሀገራችን ከዓለም አቀፍ ንግድ በተሻለ መልኩ ተጠቃሚ እንድትሆን ለማስቻልና የዓለም አቀፍ ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደትን ለማስተባበር፣ የአካባቢያዊ የንግድ ግንኙነቶችና ድርድሮች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ሀገራዊ ጥቅምን ባስጠበቀ መልኩ ለማጠናቀቅ እንዲቻል አግባብ ያላቸው አካላትን በጋራ፣ በተቀናጀና ወጥነት ባለው ሁኔታ ማስተባበር ተገቢ በመሆኑ፤
የንግድ ግንኙነትና ድርድር አካል ሆነው በተለያዩ አስፈጻሚ አካላት ሲመሩ የነበሩ ጉዳዮችን የሚመለከታቸው አስፈጻሚ አካል ተሰብስበው እንዲተዳደሩ በማድረግ በመስኩ የእውቀትና የክህሎት ሽግግር ማድረግና ብቁ የሰው ኃይልን በማፍራት ሀገራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የንግድ ግንኙነትና ድርድሮችን ከሀገራዊ ራዕይ ጋር በማስተሳሰር በመስኩ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት እንዲቻል በሚኒስትሮች ምክር ቤት አሠራር መመሪያ አንቀጽ 3 ንዑስ አንቀጽ (1) ፊደል ተራ (ሠ) መሠረት ይህ መመሪያ አውጥቷል፡፡