የመመሪያ መለያ: 645/2013
ቀን: የካቲት 22፥ 2011 ዓ.ም.
Language: Amharic

የቅጅ መብት ሮያሊቲ (የአገልግሎት ክፍያ) ተመን አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 645/2013

የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ከተቋቋመበት ዓላማ አንዱ የኮፒራይት ኢንዱስትሪውን መደገፍ እና የቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር ማህበራት ወደ ተግባር የሚገቡበትን ምቹ ሁኔታ በመፍጠር አዳዲስ የአሠራር ዘዴዎችን መዘርጋት ነው፤

ስለሆነም የጋራ አስተዳደር ማኀበራት ለጽ/ቤቱ የሚያቀርቡት የሮያሊቲ ክፍያ ቀመር ረቂቅ በቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 410/96 አንቀጽ 2(30) እና በማሻሻያ አዋጅ ቁ/872/2007 አንቀጽ 2(1) ላይ ጥበቃ ያላቸው ሥራዎች ለሀገር የሚያበረክቱትን ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሚና የሚያማዝ፣ የሀገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ እና የተጠቃሚዎችን ዓቅም ግምት ውስጥ ያስገባ መሆን ስለሚገባው፤

በመሆኑም በቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 872/2007 አንቀጽ 34(2) መሠረት ጽ/ቤቱ በጋራ አስተዳደር ማህበራት ተዘጋጅቶ የሚያቀርብለትን የሮያሊቲ ክፍያ ቀመር ረቂቅ እንደሚያፀድቅ የሚደነግግ ሲሆን ይህንንም ለመወሰን በቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 410/96 አንቀጽ 39(2) በተሠጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን

Ethiopian Intellectual Property Authority

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration