ኮንቬንሽናል ቢንጎ ጨዋታ በሀገራችን ውስጥ ባሉ ትልልቅ ከተሞች እየተዘወተረ የሚገኝ የዕረፍት ጊዜ ማሳለፊያ ጨዋታ ሲሆን፣ ሕብረተሰቡ የዕረፍት ጊዜውን በአስፈላጊው ቦታና ጊዜ እየተዝናና እንዲያሳልፍ ለማስቻል ጨዋታውን በሕግና በሥርዓት መምራት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
ጨዋታውን በሕግና በሥርዓት ከመምራት ጎን ለጎን ጨዋታው የሚካሄድበትን ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ መወሰን በማስፈለጉና ከጨዋታውም የመንግሥትን የልማት ጥረት የሚያግዝ ገቢ እንደሚገኝ በመታመኑ፤
ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደርን ለማቋቋም በወጣው ደንብ ቁጥር 160/2001 አንቀጽ 21 መሠረት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ይህን መመሪያ አሻሽሎ አውጥቷል፡፡