በአዲስ አበባ ከተማ በህብረተሰብ ተሳትፎ የአካባቢን ሰላምና ደኅንነት መጠበቅ እየተጠናከረ የመጣ አዎንታዊ ተግባር መሆኑ እና ይህን ተሳትፎ ማጠናከር በማስፈለጉ፤
የህብረተሰቡ ተሳትፎ ከሚገለጽባቸው መንገድ አንዱ በሕዝብ መዋጮ የአካባቢ ሰላምና ደኅንነት የሚጠብቁ ቅጥር ጥበቃ አካላት ቀጥሮ ማሰራት አንዱ መሆኑ እና የእዚህ ጥበቃዎች ቅጥር እና ስምሪት ወጥነት የሌለው በመሆኑ በከተማ ደረጃ በጥበቃ ላይ የሚሳተፉትን ለመለየት፣ ስምሪት ለመስጠትና ለማስተዳደር የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር74/2014 አንቀጽ 15 (2) (ሠ) እና 40 (3) መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡