የመመሪያ መለያ: 1024/2017
ቀን: መስከረም 14፥ 2017 ዓ.ም.
Language: Amharic

የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ፈቃድ እና የሬጉላቶሪ ክፍያዎች መመሪያ ቁጥር 1024/2017

ባለሥልጣኑ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ማስፋት፣ በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እና አሰራሮች የአገልግሎቶቹን የጥራት ደረጃ ማሻሻል እንዲሁም አገልግሎቶቹን ለመስጠት የሚያወጣውን ወጪ መሸፈን የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የሬዲዮ ፍሪኩዌንሲ ስፔክትረም ፈቃድ እና የመጠቀሚያ ክፍያ የሬዲዮ ፍሪኩዌንሲ ስፔክትረም ሀብት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም የሚኖረው ተገቢ ዋጋ ላይ የተመሰረተ መሆኑን እና ባለሥልጣኑ የሬዲዮ ፍሪኩዌንሲ ስፔክትረም ሀብት ለማስተዳደር፣ ፈቃድ ለመስጠት እና ለመቆጣጠር የሚያወጣውን ወጪ መሸፈን መቻሉን ማረጋገጥ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የቴሌኮሙኒኬሽን ቁጥር ፈቃድ እና የመጠቀሚያ ክፍያ የቴሌኮሙኒኬሽን ቁጥር ሀብት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም የሚኖረው ተገቢ ዋጋ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

ከኮሙኒኬሽን አገልግሎት ፈቃድ፣ ከሬዲዮ ፍሪኩዌንሲ ስፔክትረም እና ከቁጥር ምደባ እና አስተዳደር እንዲሁም ከሬዲዮ ኮሙኒኬሽን እና ከቴሌኮሙኒኬሽን መሣሪያዎች የቴክኒክ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት የሚሰበሰበውን የክፍያ መጠን በአግባቡ መወሰን በማስፈለጉ፤

ባለሥልጣኑ የሚያስከፍላቸውን የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ፈቃድ እና የሬጉላቶሪ ክፍያዎችን ውጤታማ እና ቀልጣፋ በሆነ መንገድ መሰብሰብ የሚቻልበትን ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

ባለሥልጣኑ የሚስከፍላቸውን የፈቃድ እና የሬጉላቶሪ አገልግሎት ክፍያዎች ለተገልጋዮች ግልጽ እና ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ በመታመኑ፤

እነዚህን ዓላማዎች ከግብ ለማድረስ በሥራ ላይ ያለውን የፈቃድ አገልግሎት እና የሬጉላቶሪ ክፍያዎች መመሪያዎች ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
ባለሥልጣኑ በኮሙኒኬሽን አገልግሎት አዋጅ ቁጥር 1148 /2011 አንቀጽ 26(1)፣29(1) እና 54(2) መሠረት ይህን የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ፈቃድ እና የሬጉላቶሪ ክፍያዎች መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን

Ethiopian Communication Authority

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration