የፍትሕ አካላት ባለሙያዎችን በማሰልጠን በዕውቀት፣ በክህሎትና በአስተሳሰብ ብቁ ለማድረግና ሰልጣኞችም በሥልጠና ቆይታቸው መንግሥት የያዘውን የፍትሕ ማሻሻያ ኘሮግራም በመገንዘብ የሚሰጠውን ሥልጠና በትኩረት፣ በአግባብና በሥርዓት እንዲሁም መልካም ሥነ-ምግባር በመላበስ እንዲከታተሉ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የሥልጠና ኢንስቲትዩቱ ሙያዊ ብቃትና ክህሎታቸው ያዳበሩ፣ መልካም ሥነ-ምግባርያላቸው፣ ለማህበረሰቡ አርዓያ መሆን የሚችሉ፣ በኢንስቲትዩቱ ቆይታቸው ሠላማዊ ግንኙነት ያላቸው እና የኢንስቲትዩቱን ሕግና ደንብ የሚያከብሩ የሕግና የፍትሕ አካል ባለሙያዎች እንዲሆኑ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤
የፍትሕ አካላት ባለሙያዎች ሕግና ደንብን የሚያከብሩና የሚያስከብሩ ቢሆንም በሥልጠና ኢንስቲትዩቱ በሚቆዩበት ጊዜ የኢንስቲትዩቱን ደንብና መመሪያ እንዲያከብሩ ከማስቻል በተጨማሪ በኢንስቲትዩቱ ውስጥ ሙያዊ ድባብ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፤
በሥልጠና ወቅት ሰልጣኞች የማሰልጠኛ ክፍሎችን፣ መኝታ ቤቶችን፣ ምግብ ቤቶችን፣ መዝናኛ ቦታዎችን፣ የመፀዳጃ ክፍሎችን እና ሌሎች መገለገያዎችን ሲጠቀሙ አብሮ የመሥራትና በጋራ ሀብቶች ላይ ያለ አድሎና በእኩልነት የመጠቀም መብታቸውን የመተግበር _ ክህሎት እንዲኖራቸው ማድረግ ተገቢ በመሆኑ፤
የአንድ ሰልጣኝ ሕግና ደንብን በማክበር ሥልጠና መከታተል የሌላውንም ሰልጣኝ ስምና ዝና እንዲሁም ህብረተሰቡን በፍትሕ አካሉ ላይ ያለውን አመኔታ የሚያጎለብት በመሆኑ ይህን ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ የሰልጣኞች የሥነ-ምግባርና ክትትልና የዲስኘሊን ጉዳዮች የሚታዩበት መመሪያ አውጥቶ ሥራ ላይ ማዋል በማስፈለጉ፣
ሰልጣኞች የስነ-ምግባር ግዴታዎችና የአፈፃፀማቸውን ሥነ-ሥርዓት በመመሪያ ማስቀመጡ አስፈላጊ መሆኑን በማመን ሙያው የሚፈልገውን ሥነ-ምግባር _ ከማስተማርበተጨማሪ በሥልጠና ወቅት መከተል ያለባቸው የሥነ-ምግባር መመሪያ ሥልጠና ከመጀመራቸው አስቀድሞ በግልጽ በመደንገግ ማሳወቅ አስፈላጊ በመሆኑ፤
ለፌዴራል ፍትሕና ሕግ ምርምርና ሥልጠና ኢንስቲትዩት በማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር1071/2010 አንቀጽ 16 ንዑስ አንቀጽ (2) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን የሰልጣኞች የሥነ-ምግባር መመሪያ ኢንስቲትዩቱ አውጥቷል፡፡