የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 141/2000 በህዳር ወር 2000 ዓ.ም የተቋቋመ የመንግሥት የልማት ድርጅት ሲሆን የኮርፖሬሽኑ ዋነኛ ዓላማ ተፎካካሪና አቅምን ያገናዘበ በየትራንስፖርት አገልግሎት መኖሩን ማረጋገጥ የሚቻልበትን የተቀናጀ ከፍተኛ አቅም ያለው የባቡር ትራንስፖርት ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
በመላ ሀገሪቱ ዘመናዊ የባቡር መሠረተ ልማት በመገንባት ወጪ ቆጣቢ፣ በአጭር ጊዜና በገፍ ጭነቶችን የሚያጓጉዝ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት በማስፋፋት የተመዘገበውን ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት መደገፍ እና በመላ አገሪቱ የመንገደኞች የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ማስፋፋት ደግሞ ዕቅዶቹ እና ተልዕኮዎቹ በመሆናቸው፣
ይህን ዕቅድ ለማሳካት እና የተመደበውን በጀት በአግባቡ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ለማድረግ በሥነ ምግባር የታነፁና ሙስናን እንዱሁም ኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትን የሚፀየፉ የሥራ ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎችና ሠራተኞች ያስፈልጋሉ፡፡ ሙስና፣ ብልሹ አሠራርና የሥነ ምግባር ግዴለሽነትት ፈጣን ጥራት ያለውና ወጪ ቆጣቢ የሆነ አገልግሎት እንዳይኖር በማድረግ የአንዱን መ/ቤት ራዕይና ተልዕኮ የ ሚደግፉ በመሆኑ፣
ሙስና፣ ብልሹ አሠራርና የሥነ ምግባር ጉለት እንዳይኖር በማስተማርና በመከላከል የኮርፖሬሽኑን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት የሥነ ምግባር መከታተያ አሠራርን ፤ለመወሰን በሚኒስትሮች ምክርቤት ደንብ ቁጥር 144/2000 አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ (3) መሠረት ይህ የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የሥነ ምግባር መመሪያ ወጥቷል፡፡