የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለሥልጣን ውጤታማ የሆነ የዘመናዊ ምርት ግብይት ሥርዓት ግንባቱን የማረጋገጥ፣ የምርት ገበያው አስተማማኝ፣ ግልጽ እና የተረጋጋ አሠራር እንዲኖረው የመቆጣጠር እንዲሁም በገበያው የሚሳተፉትንም ሆነ በአጠቃላይ የህብረተሰቡን ጥቅም የማስጠበቅ ኃላፊነት ያለበት በሆኑ፣
ይህን ኃላፊነት በአግባቡ ለመጣት እንዲቻል የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ሠራተኞች እና የሥራ ኃላፊዎች መልካም ሥነ ምግባር ተላብሰው እና ሕግን አክብረው ሥራቸውን እንዲያከናወኑ ለማድረግ የሚያስችል የ ሥነ–ምግባር መከታተያና መቆጣጠሪያ መማሪያ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
እነዚህን ዓላማዎች ለማስፈጸም የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለሥልጣን በማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 551/1999 (እንደተሻሻለው) አንቀጽ 6(11) እና አንቀጽ 34(2) በተሰጠው ሥልጣን መረት ይህን መመሪያ አወጥቷል፡፡