ባለስልጣኑ ዜጎች ፍትሃዊና በእኩልነት ላይ የተመሰረተ አገልግሎት የሚያገኙበት ተቋም እንዲሆንና መልካም አስተዳደርን ማስፈን በማስፈለጉ፤
ከሙስናና ብልሹ አሠራር የፀዳ፣ በሕዝብ አገልጋይነት መንፈስ የሚተጋ እና የሥነ-ምግባር መርሆዎችን ተግባራዊ የሚያደርግ ትጉህ ባለሙያ መፍጠር በማስፈለጉ፤
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን የፌደራል ስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን የስነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎችን አሠራርና አደረጃጀት ለመወሰን የወጣው መመሪያ ቁጥር 20/2013 አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ (9) መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡