በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ መዛመትን በመግታት ሊያስከትል የሚችለውን አሉታዊ የጤና፤ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ተዕጽኖ መቀነስ በማስፈለጉ፤
የኮሮና ቫይረስን መዛመትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ጥቅም ላይ የሚውሉ የጤና ግብዓቶች ማሟላት የሚገባቸውን የጥራት ደረጃ ማሟላታቸውን በማረጋገጥ በተቀላጠፈ ሁኔታ ግብዓቶቹ የገበያ ፈቃድ አግኝተው ለተጠቀሚው እንዲደርሱ ለማድረግ፤
ለህክምና አገልግሎት በጤና ተቋማት ውስጥ ለጤና ባለሙያዎች ብቻ ጥቅም ላይ እንዲውል የሚመከር የህክምና የፊት መሸፈኛ ጭምብል ህብረተሰቡም ጭምር
እየተጠቀመ በመሆኑና በዓለም አቀፍም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ የእነዚህ ምርቶች እጥረት መኖሩን ተከትሎ የምርቱ እጥረት እና የአጠቃቀም ችግር መፍታት
በማስፈለጉ፤
ይህንን ችግር ለመፍታት ጥቅም ላይ የሚውል በፋብሪካ ደረጃ ከጨርቅ የተሰራ የፊት መሸፈኛ ጭምብል ለህብረተሰብ ጥቅም ከመዋሉ በፊት ጥራቱ፤ ደህንነቱ እና ውጤታማነቱን ማረጋገጥ በማስፈለጉ፤
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 1112/2011 አንቀጽ 71(2) እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 3/2012 ለማስፈጸም በወጣ የሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ አንቀጽ 4 (6 እና 7) መሠረት ይህን ጊዜያዊ የአሠራር መመርያ አውጥቷል፡፡