የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 አንቀጽ 64 ንዑስ አንቀጽ (4) የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ከገቢ ማስገኛ ስራው ከሚያገኘው ገቢ የድርጅቱን የአስተዳደር እና የፕሮግራም ወጪዎች እንደሚያውለው የተደነገገ በመሆኑ፤
በአዋጁ አንቀጽ 63 ንዑስ አንቀጽ (3) የሃያ በመቶ ገደብ በልዩ ሁኔታ ተፈጻሚ ድርጅቶች በሚመለከት የማይሆንባቸውን ባለስልጣኑ _ መመሪያ እንደሚያወጣ የተደነገገ በመሆኑ፤
በአዋጁ አንቀጽ 5 ንዑስ አንቀጽ (2) ከአዋጁ ዓላዎች አንዱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በተመዘገቡበት ዓላማ መሠረት ሥራቸውን ማከናወናቸውን በመከታተልና የሕብረተሰቡን የላቀ ተጠቃሚነት እንደሆነ የተደነገገ በመሆኑ፤
በአዋጁ አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ (2) የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ድርጅቶቹ ሥራቸውን በሕግ አግባብ ማከናወናቸውን ለማረጋገጥ አስፈላጊውን ክትትልና ቁጥጥር የማድረግ እንዲሁም በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) የድርጅቶቹን ዓመታዊ የሥራና የገንዘብ እንቅስቃሴ ሪፖርት በአዋጁ መሠረት የመመርመር ሥልጣንና ተግባር የተሰጠው በመሆኑ፤
ከላይ ለተጠቀሱት የአዋጁ ድንጋጌዎች አፈጻጸም መመሪያ በማውጣት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሊከተሉ የሚገባቸውን አሠራር በግልጽ በመደንገግ ከባለስልጣኑ ጋር የሚኖረውን ግንኙነት ውጤታማ ማድረግ በማስፈለጉ፤
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 አንቀጽ 89 ንዑስ አንቀጽ (2) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡
Whereas; it is stipulated in Article 64 Sub-article (4) of the Civil Societies Proclamation No. 1113/2019 that a civil society organization shall use the funds obtained through income-generating activities to defray its administrative and program expenses;
Whereas; Article 63 sub-article (3) of the Proclamation provides that the Authority may issue a directive regarding organizations exempted from the twenty-percent cap;
Whereas; Article 5 sub-article (2) of the Proclamation states that one of the Authority’s objectives is to ensure utmost public benefit by supervising whether Civil Society Organizations perform their activities in accordance with their registered objectives;
Whereas; Article 6 sub-article (2), of the Proclamation granted the Authority the power to monitor and supervise that civil society organizations perform their activities in accordance with the law; and, sub-article (3) of the same article, granted the power and responsibility to examine the annual activity and financial reports of the organizations;
Cognizant of the need to issue directives for the implementation of the above-referred to provisions of the Proclamation that clearly set out procedures civil society organizations need to follow in order to ensure a fruitful working relationship with the Authority have to be put in place;
Now therefore; the Authority for Civil Society Organizations has issued this directive in accordance with the power conferred on it by virtue of Article 89 sub-article (2) of the Civil Society Organizations’ Proclamation.