የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምገባ ኤጀንሲ የዕለት ጉርስ የሌላቸው ዜጎች የማኅበራዊ ፍትሕ ማስፈንና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል የማዕከላት ምገባ አገልግለቱ የሚመራበት ወጥ የሆነ የአፈጻጸም መመሪያ ማዘጋጀት በማስፈለጉ፤
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምገባ አጀንሲ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 74/2014 አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ (2) ተራ ፊደል (ሠ) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡