በአገራችን በመካሄድ ላይ ያለውን የሕንፃ ግንባታ ሥርዓት ባለው እና ደረጃውን በጠበቀ መንገድ በመላ ሀገሪቱ ተፈጻሚነት እንዲመራ ለማድረግ፣ የሕዝብን ጤንነትና ደኅንነት ለማረጋገጥ፣ እና የሚኖረው ምቹ የግንባታ ሥርዓት እንዲኖር ለማድረግ እንዲሁም የሕንፃ ግንባታን ዝርዝር አፈጻጸምና የአሠራር ሂደቶችን ለአገልግሎት ሰጪውም ሆነ ለተገልጋዩ ግልጽ በማድረግ ቀልጣፋና ውጤታማ የሆነ አሠራር በመዘርጋት የሕንፃ አዋጁን እና ደንቡን ማስፈፀም የሚያስችል ዝርዝር መመሪያ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በህንፃ ደንብ ቁጥር 243/2ዐዐ3 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል ።