የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በአገሪቱ ኢንቨስትመንትን ማበረታታት፣ ለማስተባበርና ለማስፋፋት አዋጅ ቁጥር 769/2004ን እንደተሻሻለ እና ይህንኑ አዋጅ ለማስፈጸም ስለኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችና ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች ስለተከለለ የስራ መስኮች የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 270/2005ን እንደተሻሻለ ያወጣ በመሆኑ፤
በዚሁ ደንብ ለቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ማለትም የኮከብ ደረጃ ላላቸው ሆቴሎች የሪዞርት ሆቴልን ጨምሮ ፣ ሞቴሎች፣ ሎጆችና ሬስቶራንቶች የካፒታል ዕቃዎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው እንዲገቡ የሚፈቅዱ በመሆኑ፣
እንደ ፕሮጀክቱ ስፋት እየታየ ለቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች የካፒታል ዕቃዎችን ዓይነትና ብዛት መወሰን በማስፈለጉ፣
የኢንቨስትመንት ቦርድ በኢንቨስትመንት ዓዋጅ ቁጥር 769/2004 አንቀጽ 29/4 መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል።