የመመሪያ መለያ: 704/2013
ቀን: የካቲት 10፥ 2013 ዓ.ም.
Language: Amharic

በፌዴራል፣ በክልሎች እና አዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ተቋማት የሁለተና ዙር የዕቅድ ክንውን እንዲሁም የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድን በተሟላ መልኩ ለመተግበር የቅድመ ዝግጅት ስራ መጠናቀቁን ለመገምገም የወጣ መመሪያ ቁጥር 704/2013

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በአዲስ መልክ ከተቋቋመበት ከጥቅምት 2003 ዓ.ም ጀምሮ በርካታ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በ2003 በጀት ዓመት ሊያከናውናቸው ያቀዳቸውን ስትራቴጂክ ጉዳዮች በማስፈጸም በዘርፉ ልማትን ለማፋጠን፤ መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት የሚያስችሉ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም በከተሞች ተንስራፍቶ የሚታየውን ሥራ አጥነትንና ድህነት ለማስወገድ የሚያስችል ትክክለኛ ስትራቴጂ በመንደፍና በየደረጃው ያለው መዋቅር የጋራ የሆነ ቁልፍ ተግባር ኖሮት በዚያ ዙሪያ እንዲረባረብ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡

በከተሞች የሚታየውን የመልካም አስተዳደርአዕጦት ለመቅረፍ እንዲቻል በየተቋማቱ ያለውን አሠራር ቀልጣፋ ሊያደርግ የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት የመዘርጋት ሥራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የልማቱ ባለቤት የሆነውን የከተማ ነዋሪ በማሳተፍ መጠነ ሰፊ የአካባቢ ልማት ሥራዎችን ለማከናወን የሚያስችል የልማት ዕቅድ በማዘጋጀትና ተግባራዊነቱን በመከታተል ህብረተሰቡን የማነሳሳት ሥራ ተጀምሯል፡፡ በዘርፉ እየተከናወነ ያለው የአደረጃጀትና ሥራዎችን አናቦና አመጋግቦ ለመተግበር ያለው ጥረት የተሻለ አፈጻጸም ላይ የሚገኝ ሲሆን የማስፈጸም አቅም ግንባታን ከማጠናከር ጋር በተያያዘ ብቃት ያለው የሰው ኃይል፣ አደረጃጀትና አሠራር እንዲጎለብት በተለይም በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ (BPR) እና የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ነቅድ ትግበራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡

በመሆኑም በዘርፉ የለውጥ መሳሪያዎችን አቀናጅቶ በመተግበር በሴክተሩ የሚተገበሩ ፖሊሲዎች፣ ፕሮግራሞች፣ ፕሮጀክቶች እና ዋና ዋና ተግባራት ቀጣይነት ባለው አግባብ ክትትል፣ ግምገማና ግብረ-መልስ በማድረግ ለስኬት ማብቃት ይገባል፡፡ ለዚህም ህብረተሰቡ በላቀ ደረጃ ተጠቃሚ የሚሆንበትን ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣትና መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት የማስፈጸም አቅም ግንባታ ሥራዎች ወሳኝ ሚና ይኖራቸዋል። በመሆኑም በየደረጃው የሚታየውን የማስፈጸም አቅም ችግሮች ደረጃ በደረጃ በመፍታት ያልተማከለ አስተዳደርን ማጠናከር ያስፈልጋል፡፡

ከማስፈጸም አቅም ጋር በተያያዘ በተቋማት ውስጥ የሚደረገው እንቅስቃሴ ስኬታማ መሆን የሚችለው ሥራዎችን ለመፈጸም የሚያስችል ዘመናዊና ቀልጣፋ የአሠራር ሥርዓት ሲኖር ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ለታቀዱትን የማስፈጸም አቅም ግንባታ፤ የመልካም አስተዳደር፣ የሕዝብ ግንኙነትና ንቅናቄ እና የልማት ሥራዎቻችንን ጠንካራ የክትትል፣ ግምገማና ግብረ-መልስ ስርዓት በመዘርጋት የዕቅድ አፈጻጸማችንን ቀጣይነት ባለው መልኩ መገምገምና ግምገማውን ውጤት በፌደራል፤ ክልሎች እና አዲስ አበባና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደሮች በሚገኙ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ተቋማት፣ የሥራ ክፍሎችና ሠራተኞች እንዲያውቋቸው በማድረግ ተቋማቱ ለተሟላ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ትግበራ መብቃታቸውን የማረጋገጥ ተግባር ተለይቶ በተቀመጠ መስፈርትና ወጥነት ባለው ሁኔታ መከናወን ይኖርበታል፡፡

በዚህ አኳያ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣ አዋጅ ቁጥር 691/2003 አንቀጽ 25 ንዑስ አንቀጽ 1 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን

Ministry of Urban and Infrastructure

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration