የመመሪያ መለያ: 141/2015
ቀን: መጋቢት 1፥ 2015 ዓ.ም.
Language: Amharic

ለኢንተርፕራይዞችና አምራች ኢንዱስትሪዎች አገልግሎት እንዲውሉ የተገነቡ መስሪያ ቦታዎች ወደ ሕጋዊ አሰራር የሚመጡበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ የአፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 141/2015

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አጥ ነዋሪ ዜጎችን የስራ ዕድሎች በመፍጠር ወደ ስራ ለማሰማራት ትልቁ እና ዋነኛው ማነቆ በቂ የመስሪያ ቦታ አቅርቦት ችግር መሆኑን በመገንዘብ ይህንን ችግር በመፍታት በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ስትራቴጂን ተግባራዊ በማድረግ ድህነትና ስራ አጥነትን ለመቀነስ በስትራቴጂው ከተቀመጡት ለኢንተርፕራይዞች ከሚሰጡ የድጋፍ ማዕቀፎች ውስጥ አንዱ የመስሪያ ቦታ አቅርቦት በመሆኑ፣

በተለያየ መንገድ የተገነቡ እና ህጋዊ የአስተዳደር ስርዓት ያልተዘረጋላቸው ሼዶች፣ ተለጣፊ ሱቆች፣ መደብሮችና ሌሎች መስርያ ቦታዎች ቢኖሩም መመሪያ ተዘጋጅቶላቸው በሚፈለገው አግባብ የማይተዳደሩ ስለነበር ችግሩ ዓመታትን ያስቆጠረ የመልካም አስተዳደር ችግር በመሆኑ፣

ቀደም ሲል በጊዚያዊ የሊዝ ውል በተለያዩ ተቋማት በውል፣ በውሳኔና ያለምንም ማስረጃ ለኢንተርፕራይዝና አምራች ኢንዱስትሪዎች አገልግሎት እንዲውሉ ተላልፈው የውል ዘመናቸው የተጠናቀቀም ሆነ ያልተጠናቀቀ በግለሰብ፣ በመንግሥትና በተለያዩ በጎ አድራጎት ድርጅቶች የተገነቡ ሼዶች፣ ተለጣፊ ሱቆች፣ መደብሮች፣ መሸጫና ማሳያ ኢምፐርየም እና ህንፃዎችን ግልፅ በሆነ መንገድ ርክክብ ለማድረግና ቀደም ሲል ስራ ላይ የነበረው መመሪያ ቁጥር 77/2014 ሲተገበር ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ማሻሻያዎችን ያካተተ አዲስ መመሪያ ማውጣት አስፈላጊ ሁኖ በመገኘቱ፣

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 74/2014 አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ 2 ተራ ፊደል (ሠ) መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ

Addis Ababa City Administration Industry Development Bureau

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration