ለማዕድን ፕሮጀክቶች ከጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ነፃ ሆነው እንዲገቡ የሚፈቀዱ ተሽከርካሪዎችን ዓይነትና ብዛት ለመወሰን የካቲት 1 ቀን 1999 ዓ.ም፣ የካቲት 19 ቀን 1999 ዓ.ም. እና መስከረም 28 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የወጡትን እንደቅደም ተከተላቸው መመሪያ ቁጥር 1/1999 ዓ.ም.፣ መመሪያ ቁጥር 2/1999፣ መመሪያ ቁጥር 3/1999 ማሻሻልና በአንድ መመሪያ ማጠቃለል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር በማዕድን አዋጅ ቁጥር 52/1985 አንቀጽ 46 ንዑስ አንቀጽ (3) አዋጁን ለማስፈፀም የሚያስችል መመሪያ ለማውጣት እንደሚችል በተሠጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡