የመመሪያ መለያ: 372/2013
ቀን: ሰኔ 1፥ 2011 ዓ.ም.
Language: Amharic

የአልኮል ማስታወቂያና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 372/2013

በሀገሪቱ የአልኮል ተጠቃሚዎች ቁጥር እያደገ መምጣቱን እንዲሁም የአልኮል መጠጥን መጠቀም ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች አጋላጭ መሆኑ በጥናት ስለተረጋገጠ፤

ገደብ የሌለው የአልኮል ማስታወቂያ የአልኮል ተጠቃሚዎችን ቁጥር እንደሚጨምር በጥናትየተረጋገጠ ሲሆን ከቴክኖሎጂ መስፋፋት ጋር ተያይዞ የአልኮል ማስታወቂያ የስርጭት ስፋት፣ ይዘት፣ ዓይነት፣ የማስተላለፊያ መንገዶችንና ተደራሽነታቸውን ተገቢ በሆነ መንገድ
መቆጣጠር በማስፈለጉ፤

የሚፈቀዱ የአልኮል ማስታወቂያ መልእክቶች በተጋነነና ተገቢ ባልሆነ መልኩ በማስተላለፍ በህብረተሰቡ ላይ የሚያስከትሉትን የስነ-ልቦና ጫና ለመከላከል፤ የአልኮል ማስታወቂያ ላይ የሚተላለፉት መረጃዎች ትክክለኛ መሆናቸውንና ለመቆጣጠርና በተሳሳተ መረጃ ምክንያት ሊደርስ ከሚችል ጉዳት ህብረተሰቡን መጠበቅ በማስፈለጉ፤

በአልኮል መጠጥ ማሸጊያ ላይ በአልኮል መጠጥ ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን የጤና ችግር አስቀድሞ እንዲገለጽ በማድረግ በጤና ላይ ሊያድርስ የሚችለውን ችግር ከወዲሁ መከላከል እንዲቻል፤

የኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን በምግብና መድኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር1112/2ዐ11 አንቀጽ 71 (2) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን

Ethiopian Food and Drug Authority

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration