የመመሪያ መለያ: 838/2014
ቀን: መስከረም 20፥ 2014 ዓ.ም.
Language: Amharic

በዱር እንስሳት የተጠበቁ ቦታዎችን ከህዝብ እና ከግል አጋርነት ጋር ለማስተዳደር የወጣ መመሪያ ቁጥር 838/2014

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ሀብት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም እንዲሁም የዱር እንስሳት ጥበቃ ቦታዎች ስርዓተ አያያዝን የግል ዘርፉና የህብረተሰቡ ተሳትፎን በማጎልበት እየደረሰባቸው ካለው አደጋ እንዲያገግሙ በማድረግ ሃብቱን በተገቢ ሁኔታ መጠበቅ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የጥበቃ ቦታዎች ሥርዓተ-አያያዝ ከፍተኛ መዋእለ ንዋይ የሚጠይቅና ይህም በመንግሥት ብቻ መሽፈን የማይቻል በመሆኑና የግል ዘርፉንና ህብረተሰቡን ማሳተፍ በማስፈለጉ፤

የዱር እንስሳት ሀብቱን ለመጠበቅና ለማልማት የሚያስችል አጋርነትን በማስፋፋት እና አካባቢያዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች ይበልጥ በማሳደግ አገሪቱ በዘርፉ ተወዳዳሪ እና ተመራጭ የምትሆንበትን መንገድ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፤

ኮሚሽኑ በአዋጅ ቁጥር 541/1999 አንቀጽ 6 እና 13 ንዑስ አንቀጽ 1 እንዲሁም አንቀጽ 17 ንዑስ አንቀጽ 2፣ በአዋጅ 575/2000 አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ 1 እና 12 እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 1097/2011 አንቀጽ 33/25/ሐ መሠረት ይህን በመንግሥትና በግል አጋርነት የዱር እንስሳት ጥበቃ ቦታዎችን ለማስተዳደር የሚያስችለውን ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአካባቢ፣ የደን እና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን

Environment, Forest and Climate Change Commission

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration