የመመሪያ መለያ: 641/2013
ቀን: ታህሳስ 21፥ 2006 ዓ.ም.
Language: Amharic

የንግድ ምልክትን ለመመዝገብ የወጣ ተጨማሪ መመሪያ (መመሪያ ቁጥር 641/2013)

በሃገራችን የተጠናከረ የንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አሠራር መኖር ፍትሃዊ የንግድ ውድድርን በማስፈን የንግዱ ማኅበረሰብ መልካም ስምና ዝናውን ጠብቆ በገበያ ላይ ተወዳዳሪ ለመሆን ከማስቻሉም በላይ በህገወጥ መንገድ በገበያ ላይ መሳከርን በመፍጠር ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት የሚፈልጉትን አካላት በማዳከም የሸማቾችን ጥቅም የማስጠበቅና የውጭ ኢንቨትመንትን በመሳብ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማፋጠን የሚያስችል ስርዓት ነው፡፡

ይህንን ዓላማ ለማሳካት ያስችል ዘንድ የንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 501/1998 የወጣ ሲሆን አዋጁን ለማስፈጸም የሚያስችል ማስፈጸሚያ ደንብ 273/2005 በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቆ ተግባራዊ በመሆኑ አዋጁንና ይህን ደንብ መሠረት በማድረግ አዋጁ ከመውጣቱ በፊት የተመዘገቡ ሁሉንም የንግድ ምልክቶች እንደገና መመዝገብ የግድ የሚል በመሆኑ፤

አዋጁ ከወጣ በኋላ የተመዘገቡ የንግድ ምልክቶችንም ቢሆን በአዋጁ በተቀመጠው ጊዜና በደንቡ የተመላከቱጉዳዮችን ያካተተ የምዝገባ ሰርተፊኬት መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ፥

በደንቡ አንቀጽ 59 መሠረት ጽ/ቤቱ ማስፈጸሚያ መመሪያ ለማውጣት በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የንግድ ምልክት ምዝገባ የሚመራበትን ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ አዘጋጅቶ የንግድ ምልክት እንደገና ምዝገባ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ሆኖም በዚህ የምዝገባ ሂደት የታዩ ግልጽነት የጎደላቸው ጉዳዮችን በማስተካከል የንግድ ምልክት የምዝገባ ማስተካከያ ስራዎችን በአጭር ጊዜ ማከናወን እንዲቻል ይህ ተጨማሪ የአፈጻጸም መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን

Ethiopian Intellectual Property Authority

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration