የመመሪያ መለያ: 70/2014
ቀን: ሰኔ 1፥ 2012 ዓ.ም.
Language: Amharic

የአዲስ አበባ መሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክት መስተንግዶ መመሪያ ቁጥር 70/2014

መሬት ለአንድ ሀገር ማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ወሳኝ የሆነ ውሱን የተፈጥሮ ሀብት እንደመሆኑ መጠን መንግሥት ይህንን ውሱን ሀብት ፍትሐዊ፣ ግልጽ እና ተጠያቂነትን ባሰፈነ አሠራር ጥቅም ላይ መዋሉን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል፡፡

ይህንን በተግባር ለማዋል ግልጽ የአሠራርና የሕግ ማዕቀፍ ከአጠቃላይ የሀገሪቱ የልማትና የመልካም አስተዳደር አቅጣጫዎችን መሠረት በማድረግ አዘጋጅቶ መተግበር ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ አንፃር በአገራችን የመሬት የባለቤትነት ጉዳይ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገመንግሥት በግልጽ እንደሰፈረው የሕዝብና የመንግሥት ሀብት ሲሆን መሸጥ መለወጥ እንደማይቻል ተደንግጓል፡፡

ከዚህ ጎን ለጎን ሀገሪቷ ከምትከተለው የነፃ ገበያ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጋር የሚጣጣም መሬትን የመጠቀም መብት በሊዝ ማስተላለፍ እንዲቻል የሊዝ አዋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1986 ዓ.ም አዋጅ ቁጥር 89/1986 ዓ.ም የወጣ ሲሆን ይህን አዋጅ የነበሩበትን ክፍተቶች በመለየት እንደገና በ1994 ከዚያም በ2ዐዐ4 አዋጅ ቁጥር 721/2ዐዐ4 ዓ.ም ወጥቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ይህን አዋጅ ተከትሎ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ደንብና መመሪያዎች ያወጣ ሲሆን፣ ደንቡን በተሟላ ደረጃ ተግባራዊ ማድረግ እና የተጀመረውን ለውጥ በተሟላ አሠራር ለመደገፍ እንዲቻል፣ ደንቡና መመሪያዎቹ ሲዘጋጁ በዝርዝር እንዲታይ የታለፈው ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ኘሮጀክቶች መስተንግዶን በተመለከተ ደግሞ የከተማው አስተዳደር ካቢኔ በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ 361/1995 ዓ.ም አንቀጽ 14/1/ረ እና አንቀጽ 23/1/1 መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ

City Government of Addis Ababa Land Development and Management Bureau

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration