የመመሪያ መለያ: 150/2016
ቀን: የካቲት 18፥ 2016 ዓ.ም.
Language: Amharic

የአዲስ አበባ ከተማ ተማሪዎች የዲሲፒሊን መመሪያ ቁጥር 150/2016

ተማሪዎች በትምህርት ቤት በጥሩ ሥነ-ምግባር በመታነጽ ለራሳቸው ለማህበረሰባቸው እና ለሀገራቸው ጠቃሚ ዜጋ ሆነው ሊቀረጹ የሚገባ በመሆኑና አሁን እየታየ ያለው የተማሪዎች የሥነ-ምግባር ችግር በመማር ማስተማሩ ሂደት ላይ የራሱን አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረ የመጣ በመሆኑና ይህንን ችግር ከወዲሁ ማስተካከልአስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

ተማሪዎች መልካም ምግባርን በመላበስ ለሀገራቸውና ለወገናቸው ተቆርቋሪ ችግር ፈችና መልካም ስነ ምግባር ያላቸው ዜጐች ሆነው እንዲቀረጹ ለማስቻልየትምህርት ቤታቸውን ሕግና ደንብ በማክበር በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ማድረግ በማስፈለጉ፤

በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች የመማር ማስማር ሂደቱ ሳይታወክ እና የትምህርት ቤቱ ሰላምና ደኅንነት ተጠብቆ እውቀት የሚቀስሙበት ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት ሥልጣንና ተግባራቸውን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 74/2014 አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ (2) ተራ ፊደል (ሠ) መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ

Addis Ababa City Administration Education Bureau

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration