የመመሪያ መለያ: 25/2013
ቀን: ሰኔ 1፥ 2009 ዓ.ም.
Language: Amharic

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የሥራ መሪዎች መተዳደሪያ መመሪያ ቁጥር 25/2013

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አዲሱን አደረጃጀት መነሻ በማድረግ እና ነባሩን የሥራ መሪዎች መተዳደሪያ መመሪያ ከአዲሱ አደረጃጀት ጋር ማጣጣም በማስፈለጉ እንዲሁም ነባሩ የሥራ መሪዎች መተዳደሪያ መመሪያ በዲሲኘሊን አወሳሰን ላይ ያላካተታቸው ጉዳዮች በመኖራቸው በአፈፃፀም ላይ ችግር በማስከተሉና ወቅታዊ ሁኔታን ባገናዘበ መልኩ ለጥቅማጥቅም ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ መስጠት አስፈሊጊ በመሆኑ፣

የሥራ መሪዎች የመንግሥትን የልማት አቅጣጫ መሠረት አድርገው በከተማ ደረጃ ሊኖር የሚገባውን የመንገድ መሰረተ ልማት ሥራ በመምራት ምርታማና ውጤታማ እንዲሆኑ እና መብታቸውንና ግዴታቸውን በግልጽ አውቀው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ እና ለአሠራር አመቺ የሆነ መተዳደሪያ መመሪያ አዘጋጅቶ ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፣

በአዱስ አበባ ከተማ መንገድች ባለሥልጣን ማቋቋሚያ መመሪያ ቁጥር 7/1990 አንቀጽ 18 ንዐስ አንቀጽ 1(ቀ) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ይህን የሥራ መሪዎች መተዳደሪያ መመሪያ አዘጋጅቶ አቅርቧል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን

Addis Ababa City Roads Authority

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration