የመመሪያ መለያ: 56/2013
ቀን: ግንቦት 1፥ 2001 ዓ.ም.
Language: Amharic

የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ኤክስቴንሽን ፖኬጅ የአፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 56/2013

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ መንግሥት በሃገሪቷ ፈጣንና ዘላቂነት ያለው ልማት ለማረጋገጥና ማኅበራዊ ደኅንነትን ለማስፈን የሚያስችሉ የተለያዩ ልማታዊና ማኅበራዊ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን ቀርጾ በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች እንዲተገበሩ በማድረግ የሚያበረታቱ ውጤቶችን እያስመዘገበ ይገኛል፡፡

ከማኅበራዊ ዘርፎች አንዱ በሆነው በጤና ሴክተርም ህብረተሰቡ ጤናው ተጠብቆ በልማት ሂደቱ በሙሉ አቅሙ ተሳታፊ ሊሆን የሚያስችል ጤናማ እና አምራች ዜጋን ለማፍራት፤ በዚህም ፈጣንና ቀጣይነት ያለው እድገት በሃገሪቷ ለማረጋገጥ አዲስ የጤና ፖሊሲ ቀርፆ ለተግባራዊነቱም ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

የጤና ፖሊሲው ከሃገሪቷ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ጋር ተጣጥሞ ሊፈጸም የሚችል፤ በዋናነት በሽታን በመከላከልና ጤናን በማጐልበት ላይ እንዲያተኩር ተደርጎ የተቀረፀ ነው፡፡ ፖሊሲውን ለመተግበር የሚያስችሉ ሴክተር አቀፍ እስትራቴጂዎች እና አራት የአምስት ዓመት የልማት እቅዶች ተቀርፀው እንቅስቃሴ ውስጥ የተገባ ሲሆን እስከ አሁን ባለው ጊዜ ሁለት የአምስት ዓመት የጤና ሴክተር የልማት እቅድ ምዕራፎች ተፈፃሚነት አግኝተው በአሁኑ ጊዜ ሦስተኛው ምዕራፍ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡

ከሁለተኛው ምዕራፍ የጤና ሴክተር ልማት ስትራቴጂክ ዕቅድ ጀምሮ በሁሉም የሃገሪቷ የገጠር ወረዳዎች በትግበራ ሂደት ውስጥ ያለው የገጠር ጤና ኤክስቴንሽን ፖኬጅ ነው፡፡ የፖኬጁ ዋና ዓላማ ከጤና ተቋማት ርቆ የሚገኘውን የህብረተሰብ ክፍል የመሠረታዊ ጤና አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግና የጤና አገልግሎቱን ስርጭት ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ በዚህም የጤና ፖሊሲውን ዓላማና ግቦች ለማሳካት ነው፡፡

ይህ ፖኬጅ ሃገሪቷ እንድታሳካ የሚጠበቅባትን የምዕተ-ዓመቱ የልማት ግቦች በተፋጠነ ጊዜና ወጭ ቆጣቢ በሆነ አኳኋን ለማስፈፀም ውጤታማነቱ ከመረጋገጡም በላይ የህብረተሰቡን ጤና ከማጎልበትና በሽታን ከመከላከል አንጻር በአገር አቀፍ ደረጃ ብዙ ተሞክሮዎች የተገኙበት ነው::

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ቢሮ

Addis Ababa City Administration Health Bureau

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration