የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የመሰረዊ አሠራር ሂደት ለውጥ በማድረግ ወደ ሙሉ ትግበራ መግባታቸው የሚታወቅ ነው በመሆኑም:-
• አሁን በሥራ ላይ ያለው የቋሚ መንግሥት ሠራተኞች የምልመላና መረጣ ቅጥር አፈጻጸም መመሪያ በመሠረዊ የአሠራር ሂደት ለውጥ ጥናት ያልተቃኘ በመሆኑ፣
• የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት መ/ቤቶች ሰው ኃይል አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደቶች ለመሥሪያ ቤቱ አስፈላጊውን የሰው ኃይል ቅጥር ፈጻሚዎች በመሆናቸው እንዲሁም የቅጥር ሥርዓቱ አዲስ በተጠናው የመሠረታዊ አሠራር ሂደት ለውጥ መሠረት እንዲከናወንና ወጥነት ያለሁ እንዲሆን በማስፈለጉ፣
•ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንግሥት መ/ቤቶች የሚገባው የሰው ሀብት ምልመላና መረጣ በብቃት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን በማስፈለጉ፣
•አመልካቾች በችሎታቸው ለመወዳደር እኩል ዕድል የሚያገኙበትን የአሠራር መርህ መዘርጋቱ ተገቢ በመሆኑ፣
•የመምርጫ ፈተናዎች የሚፈለገውን የብቃት ደረጃ የሚለኩና አስተማማኝ እንዲሆኑ በማስፈለጉ፣
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቀጥር 6/2000 በአንቀጽ 16/3 መሠረት ይህ የቅጥር አፈጻጸም መመሪያ እንዲዘጋጅ ተደርጓል::