በገቢ ግብር አዋጅ 979/08 አንቀጽ 3 ንዑስ አንቀጽ 2 ላይ የታክስ ባለስልጣኑ ታክስ ከፋዩ የሚያሳውቀውን ግብር ወይም የሚያገኘውን ሌላ መረጃ መሠረት በማድረግ ለግብር ዓመቱ የግብር ከፋዩ ደረጃ የተለወጠ መሆን አለመሆኑን እንደሚወስን በተመለከተው መሠረት፣ በዚሁ የገቢ ግብር የመሸጋገሪያ ድንጋጌ አንቀጽ 101 ንዑስ አንቀጽ 5 እና በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 መሠረት ይህ አማካይ የቀን ገቢ ግምት መረጃ ማሰባሰቢያ ማስፈጸሚያ መመሪያ ወጥቷል፡፡