የመመሪያ መለያ: 39/2013
ቀን: ጥቅምት 2፥ 2010 ዓ.ም.
Language: Amharic

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንገድ ፍጥነት ወሰን መመሪያ ቁጥር 39/2013

በአዲስ አበባ ከተማ በትራፊክ አደጋ ምክንያት በእግረኞች ላይ እየደረሰ የሚገኘው ከፍተኛ የሆነ የሞት፣ የአካል መጉደል እና የህሊና (የሞራል) ጉዳት ለመቀነስ ልዩ ትኩረት በመስጠት አፋጣኝ መፍትሄ መስጠት አስፈላጊ ጉዳይ እንደሆነ የታመነበት በመሆኑ፤

እየጨመረ የሚገኘው የትራፊክ አደጋ እና በዚህም ምክንያት እየደረሰ ያለውን ሰብዓዊ ጉዳትና ቁሳዊ ኪሳራ ለመከላከል ታስቦ የተቀረጸው የመንገድ ደኅንነት ስትራቴጅ ሰነድ ታሳቢ ያደረገ እርምጃ ተግባራዊ ማድረግ በማስፈለጉ፤

ከተሸከርካሪ ፍጥነት ጋር በተያያዘ የሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች በየጊዜው እየጨመሩ የሚገኙ መሆኑን በጥናት በመረጋገጡ እና አደጋዎችን መቀነስ ታሳቢ ያደረገ የፍጥነት ወሰን መደንገግ በማስፈለጉ፤

የከተማችን ሁለተናዊ ዕድገት በተለይ የሕዝብ ቁጥር መጨመርና የአንቅስቃሴ መስፋፋት እንዲሁም የተሻሻሉ የመንገድ መሰረተ ልማቶችንና የዘመናዊ ተሸከርካሪዎች ፍጥነት ግምት ውስጥ ያስገባ በባለሞተር ተሸከርካሪ እና በመንገዶች አይነትና ደረጃ የሚያገለግል እንደየሁኔታው በየጊዜው ሊከለስ የሚችል የፍጥነት ወሰን ሊኖር እንደሚገባ በመታመኑ፤

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላትን እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 35/2004 አንቀጽ 9 ንዑስ ቁጥር 2 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን የአዲስ አበባ ከተማ የባለሞተር ተሽከርካሪ የመንገድ ፍጥነት ወሰን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ

Addis Ababa City Administration Transport Bureau

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration