የመመሪያ መለያ: 87/2014
ቀን: ሰኔ 1፥ 2013 ዓ.ም.
Language: Amharic

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የደረጃ ዕድገት አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 87/2014

ለተቋሙ ውጤታማነት የላቀ የሥራ አፈጻጸም፤ ዕውቀት፤ ብቃትና ሥነ ምግባር ያላቸውን ሠራተኞች ከፍ ወዳለ ደረጃ በማምጣት ሥራን የተሻለ አቅም ባላቸው ሠራተኞች ማሠራት አስፈላጊ በመሆኑ፤

የደረጃ ዕድገት የሥራ አፈጻጸምን ለማሻሻል፣ የሠራተኛውን የሥራ ፍላጎት ለማነሳሳትና ሠራተኛው በመ/ቤቱ ላይ ያለውን እምነት ከፍ ለማድረግ ከሚያስችል የማትጊያ ስልቶች አንድ በመሆኑ፤

ቀደም ሲል ሲሰራበት የነበረውን የደረጃ ዕድገት አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 108/2007 በትግበራ ወቅት የታዩ ጉድለቶችን ለማረምና ቢሮዉ ከደረሰበት ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ለአፈጻጸም በሚያመች መንገድ ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣

የሰው ኃይል እንዲመደብባቸው የሚያስፈልጉ ክፍት የሥራ መደቦችን ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች በወቅቱ እንዲሸፈኑ ለማድረግ፣ በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሠራተኞች አስተዳደር ደንብ ቁጥር 99/2010 አንቀጽ 9 (4) መሠረት ቢሮዉ ይህን የደረጃ ዕድገት አፈጻጸም መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ

Addis Ababa City Administration Revenues Bureau

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration