የመመሪያ መለያ: 80/2014
ቀን: ጥቅምት 1፥ 2014 ዓ.ም.
Language: Amharic

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የትርፍ ሰዓት ክፍያና የማካካሻ ዕረፍት አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 80/2014

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የከተማው ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን ገቢ የመሰብሰብና ቀልጣፋ አገልግሎት የመስጠት ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት እንዲችል ከመደበኛ የሥራ ሰዓት በተጨማሪ በትርፍ ሰዓት መከናወን ያለባቸውን ሥራዎች ለማስፈፀም የሚረዱ የትርፍ ሰዓት ክፍያ ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤

የሥራ ኃላፊዎች ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ አላቸው ብለው የሚያምኑባቸውን ሥራዎች በጥንቃቄ በመለየት በትርፍ ሰዓት ሊያሰሩ የሚችሉበትን ዕድል ለመፍጠር ሕጋዊ የክፍያ ማዕቀፍ ማበጀት በማስፈለጉ፤

በተቋሙ ልዩ ባሕርይ ምክንያት በመደበኛ የሥራ ሰዓት ሊጠናቀቁ የማይችሉ መሆናቸው የተረጋገጠላቸውን ሥራዎች በትርፍ ሰዓት እንዲሰሩ በማድረግ የተቋሙን የዕቅድ አፈፃፀም ማሳደግ ተገቢ በመሆኑ፤ በተቋሙ የሥራ ባህርይ አስገዳጅነት ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጭ ለሚሰሩ ሠራተኞች እንደምርጫቸው የትርፍ ሰዓት ክፍያ መፈፀም ወይም የማካካሻ ዕረፍት መስጠት ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ፣

ተቋሙ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ራሱን ችል ሰለወጣ በሥራ ላይ የነበረውን የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የትርፍ ሰዓት ክፍያ አሠራር በማስቀረት በአፈጻጸም ይታዩ የነበሩ ክፍተቶችን የሚያርም ከትርፍ ሰዓት ክፍያ ጋር በተያያዘ ለሚያነሱ ቅሬታዎች ትክክለኛ ምላሽ የሚሰጥ አሠራር ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤ በትርፍ ሰዓት እንዲሰሩ የሚደረጉ ሠራተኞችን ፍላጎት እንደ የሥራው ባሕርይ አስገዳጅነት በትርፍ ሰዓት ክፍያ ወይም በማካካሻ ዕረፍት በማሟላትና የሥራ ተነሳሽነታቸውን መጠበቅ ተገቢ ስለሆነ፤

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴክተር መ/ቤቶችን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 64/2011 አንቀጽ 39/11 እና በደንብ ቁጥር 99/2010 አንቀጽ 47 መሠረት ተቋሙ ይህን የሠራተኞች የትርፍ ሰዓት ክፍያና የማካካሻ ዕረፍት አፈፃፀም መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ

Addis Ababa City Administration Revenues Bureau

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration