የዕድሮችና በየደረጃው ያሉ የእድር ምክር ቤቶች ህጋዊ ሆነው እንዲንቀሳቀሱ በማድረግ፣ አደረጃጀቶችን በማጠናከር፣ አቅማቸውን በመገንባትና በቅርበት በመደገፍ መሥራት እንዲችሉ ምቹ ሁኔታ መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
እድሮች ከቀብር ባሻገር ወደ ልማት ለመግባት እንዲችሉ፣ ታሪካዊና ባህላዊ እሴታቸውን ጠብቀው ለትውልድ እንዲሸጋገር ለማድረግ እንዲሁም ለማኅበራዊ ችግር እና ለማኅበራዊ ጠንቆች ተጋላጭየሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማገዝ ማኅበራዊ ኃላፊነታቸው እንዲወጡ ለማስቻል የሚያግዝ ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤
እድሮች እና የእድር ምክር ቤቶች የሚመዘገቡበት እና እውቅና የሚያገኙበት ስርኣት መዘርጋት በማስፈለጉ፤
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፤ ህጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስፈፃሚ አካላት ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 74/2014 ዓ.ም አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ (2) ተራ ፊደል (ሠ) መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡