የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ በከተማው የአስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሞተር ብስክሌቶች በከተማው ነዋሪና የትራፊከ እንቅስቃሴ ላይ የሚፈጥሩትን አላስፈላጊ ተፅዕኖ ለመቀነስ በሞተር ብስክሌት ፈቃድና ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 02/201 መሠረት የፈቃድና ቁጥጥር ስርዓት መዘርጋቱ ይታወቃል፡፡
ስለሆነም ይህ መመሪያ ተግባራዊ ሲደረግ የተለያዩ ማኅበረሰብ ክፍሎች በኣዲስ ኣበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ተጠሪ ተቋማት የተሽከርካሪ ሰሌዳ የወሰዱ እንዳሉ ይታወቃል። በከተማዋ በሞተር ብስክሌት የሚደረግ እንቅስቃሴ በመገደቡ ምክንያት እነዚህ የማህበረሰቡ ኣካላት ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር እንዳያስከትል ማድረግ ኣሰፈላጊ ነው። ይህንን ችግር ለመቅረፍ የቁጥጥር ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ አገልግሎቱ ህጋዊ አደረጃጀትና ፍቃድ ኖሮት ማስቀጠል የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት አስፈገላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
የሞተር ብስክሌት የመከታተያ ስርዓት ቴክኖሎጂ በማስገጠም በማህበር በመደራጀትም በግል የተለያዩ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተግባራትን ለማከናወን ፈቃድ የሚጠይቁ አካላትን ለማስተናገድ ዝርዝር የአሠራር መመሪያ እንደሚያዘጋጁ ኃላፊነት የሚጥል በመሆኑና የሚገጠመውን የሞተር ብስክሌት መከታተያ ስርዓት ቴክኖሎጂ ዝርዝር መግለጫ (Specification) በመመሪያ መወሰን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
የአዲስ አበባ አስተዳደር በከተማው ውስጥ መንገደኞች፣ እቃዎች፣ በንግድ ትራንስፖርት ስለሚጓጓዙበት ሁኔታ መመሪያ ማውጣትና አፈጻጸሙን መከታተል እንዲችል በፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን በተሰጠው ውክልና መሠረት በአዋጅ ቁጥር 468/1997 አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ 1(ረ) እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስፈፃሚ አካላትን እንደገና ለማደራጀት፣ ሥልጣንና ተግባራቸውን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 64/2011 አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ 3(ሠ) በሞተር ብስክሌት የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥበትን አደረጃጀትና አሠራር ለመወሰን ይህን መመሪያ አውጥቷዋል፡፡