የመመሪያ መለያ: 126/2014
ቀን: ጥር 18፥ 2014 ዓ.ም.
Language: Amharic

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቅርሶች ጥበቃና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 126/2014

ቅርስ የሰው ልጅ የእድገት ሂደት፣ ባህልና ታሪክ መገለጫ ስለሆነ ህብረተሰቡን አሳታፊ ያደረገ የቅርስ ጥበቃና አስተዳደር ስርዓት በመዘርጋት ቅርሶች ላሉበት አካባቢ ህብረተሰብ ብሎም ለሀገር አቀፍ ዘላቂ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ማስቻል በማስፈለጉ፤

በመሆኑም ባህል፣ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ ክልል ውስጥ የሚገኙ ቅርሶችን በመመዝገብ፣ በማጥናት፣ በመንከባከብ፣ በመጠበቅ፣ በማስጠበቅ እና በማልማት የቅርስነት እሴታቸው እንደተጠበቀ በማቆየት ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ አስፈላጊ በመሆኑ፤

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ቅርሶችን በብሔራዊ እና በክልል ቅርስነት መመደቢያ አዋጅ ቁጥር 839/2006 አንቀጽ 5 ንዑስ አንቀጽ (2) ፣ (3) እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 74/2014 ዓ.ም አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ (2) ተራ ፊደል (ሠ) መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ

Addis Ababa City Administration Culture, Arts and Tourism Bureau

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration