የመመሪያ መለያ: 60/2013
ቀን: ሰኔ 17፥ 2006 ዓ.ም.
Language: Amharic

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጋራ ህንፃ ኮንደምንየም ቤት አሰጣጥና አጠቃቀም መመሪያ ቁጥር 60/2013

የሀገራችን የጤና ፖሊሲ በመከልከል ላይ የተመሰረተ እና የራሱን ጤና ሊያመርት የሚችል ሕብረተሰብ መፍጠር ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በከተማዋ የሚስተዋለውን ከፍተኛ የጤና ችግር ለመቅረፍና ለሕብረተሰቡ ደረጃውን የጠበቀ፣ ጥራት፣ ተከታታይነትና ቀጣይነት ያለውን የጤና አገልግሎት ለማቅረብ ይቻል ዘንድ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት የተለያዩ የሆስፒታል ማስፋፊያ ግንባታዎችን በማከናወን፣ አዳዲስ ሆስፒታሎችን እና ጤና ጣቢያዎችን በመገንባት ከፍተኛና ውጤታማ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡

የጤና ተቋማትን ከማስፋፋት ባሻገር የተለያዩ ደረጃ ያላቸውን እስፔሻሊስት እና ጠቅላላ ሃኪሞችን እየሰጡ ያለውን የጤና አገልግሎት ጥራት ለማስጠበቅ ከፍተኛ እርብርብ እየተደረገ ይገኛል፡፡

በመሆኑም በየሆስፒታሉ ተመድበው እየሰሩ ያለትንና ወደፊትም በዝውውርም ሆነ በቅጥር ወደ አዲስ አበባ ጤና ተቋማት/ የሚመደቡ ከፍተኛ ባለሙያዎችን /ሃኪሞችን ተቀብሎ በሙለ አቅማቸው እንዲሰሩና ሆስፒታሎቻችንም ለሀኪሞች ምቹና ተስማሚ የስራ ቦታ እንዲሆኑ እንዲሁም ከፍተኛ የጤና ባለሙያዎች በተመደቡበት ቦታ ተረጋግተው ለረዥም ጊዜ በሙያቸው ሕብረተሰቡን እንዱያገለግሉ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን እንዲከበሩላቸው ተደርጓል፡፡

ከነዚህ ጥቅማጥቅሞች ውስጥ አንደና ዋነኛው የሃኪሞች የመኖሪያ ቤት እንዲያገኙ ማድረግ ነው፡፡ በዚሁ መሠረት የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ 250 ኮንደሚንየም የጋራ መኖሪያ ቤት በመረከብ በወቅቱ ተመድበው እየሠሩ ለነበሩ ሃኪሞች በኪራይ እንዲገለገሉበት ተደርጓል፡፡ ወደፊትም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኤጀንሲ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን እየጠየቅን ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው እየጨመረ ለሚመጣው የከፍተኛ ሃኪሞች አገልግሎት እንዲውል ያደርጋል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ቢሮ

Addis Ababa City Administration Health Bureau

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration