የመመሪያ መለያ: 90/2014
ቀን: ሚያዝያ 1፥ 2014 ዓ.ም.
Language: Amharic

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ቢሮ የመሰረተ ልማት ቅንጅት ግንባታ ፍቃድ ቁጥጥር የህንፃ መመሪያ ቁጥር 90/2014

በአገራችን በመካሔድ ላይ ያለው የግንባታ ሥርዓት ባለው እና ደረጃውን በጠበቀ መንገድ እንዲመራ ለማድረግ፣ የሕዝብን ጤንነት፣ ደኅንነትና ብልጽግና ለማረጋገጥና በመላ ሀገሪቱ ተፈፃሚነት የሚኖረው ምቹ የግንባታ ሥርዓት እንዲኖር ለማድረግ እንዲሁም የግንባታ የሥራ ሂደቶችና ዝርዝር አፈፃፀም ለአገልግሎት ሰጪም ሆነ ለተገልጋዩ ግልጽ በማድረግ ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ተጠያቂነት ያለበት የአሠራር ሥርዓት ለመዘርጋት በፌዴራል መንግሥት የወጣውን የኢትዮጵያ ሕንፃ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ በከተማው ውስጥ ማስፈጸም የሚያስችል የሕንጻ መመሪያ ቁጥር 5/2003 (ከነማሻሻያው) ቢኖርም ካለው ነባራዊ ሁኔታ እና አሠራር የተሻሻለ የሕንጻ መመሪያ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ መመሪያው ከከተማው አስተዳደር መዋቅራዊ ፕላን መርሆች፣ የአፈፃፀም ስልቶች እና ከመሰረተ ልማት ቅንጅት፤

ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ስርዓት ጋር እንዲጣጣምና የሚመለከተው የመሰረተ ልማት ቅንጅት፣ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ሥልጣንና ተግባሮቹን ለመወጣት የሚያስችል የአፈፃፀም ሥርዓት እንዲኖረው ማድረግ በማስፈለጉ፤ በአዲስ አበባ ከተማ መሪ ፕላን ፕሮጀክት ጽ/ቤት በቀረበው የመመሪያ ረቂቅ ላይ ባለድርሻ አካላትና በከተማው ካቢኔ ሰብሰባዎች የተሰጡትን ግብረ መልሶች ከግምት በማስገባት እንዲሁም ከኢትዮጵያ የሕንጻ ስታንዳርዶች ጋር ማገናዘብ ስላስፈለገ የመመሪያው ይዘት የበለፀገና ሲያጋጥሙ ለቆዩ ችግሮች የመፍትሔ ምላሾችን እንዲያካትት በማድረግ ዝግጅቱ የተጠናቀቀ በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ህንፃ አዋጅ ቁጥር 624/2001 በተደነገገው መሠረት ከከተማው ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር የተገናዘበ ሙያዊ እና ሳይንሳዊ አስገዳጅ መሥፈርቶችን ማለትም በኢትዮጵያ የሕንጻ ስታንዳርዶች መሠረት በማድረግ የግንባታና የመሰረተ ልማት ቅንጅት፣ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር መመሪያ ለማውጣት እና ለማስፈፀም ለከተማው አስተዳደር በተሰጠው ሥልጣንና በከተማው አስተዳደር የመሰረተ ልማት ቅንጅት፣ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 50/2009 በተደነገገው መሠረት እንዲሁም የኢትዮጵያ ህንፃ አዋጅ እና መመሪያ ቁጥር 5/2003ን መሠረት በማድረግ ይህ የአዲስ አበባ ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሰረተ ልማት ቅንጅት፣ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የተሻሻለ መመሪያ ቁጥር 2/2010 ተብሎ ወጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ኮንስትራክሽን ሥራዎች ቢሮ

Addis Ababa Design And Construction Works Bureau

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration