የመመሪያ መለያ: 406/2013
ቀን: ግንቦት 1፥ 2008 ዓ.ም.
Language: Amharic

የነጥብ የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናትን ለመተግበር የተዘጋጀ የድልድል አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 406/2013

የሀገሪቷን ራዕይ ለማሳካት መንግሥት የልማት ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ቀርጾ ተግባራዊ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ የአንድን ሀገር ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች የማስፈጸም ኃላፊነት የተጣለባቸው ልዩ ልዩ መንግሥታዊ ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ውጤት ማሳካት ይችሉ ዘንድ በእውቀቱ የበለጸገና በአመለካከቱ የሕዝብ አገልጋይነት ስሜትን የተላበሰ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት የሚሰጥ፣ በቅንነትና በታማኝነት ሀገራዊ ተልዕኮውን ለማሳካት በቁርጠኝነት የተሰለፈ የመንግሥት ሠራተኛ መገንባት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡

በመሆኑም መንግሥት የሀገሪቱን የሲቪል ሰርቪስ ችግሮች በማጥናትና ዘርፉ ያሉበት ችግሮች በመለየት የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራምን ነድፎ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ሲሆን ችግሩን ስር ነቀል በሆነ መልኩ በአሠራር፣ በአደረጃጀትና በአመለካከት ለመቀየር የሚያስችል የለውጥ መሣሪያ በመጠቀም በፌደራል፣ በክልል እና በከተማ አስተዳደር ደረጃ ባሉ የመንግሥት ተቋማት የለውጥ ፕሮግራሞች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ የለውጥ ፕሮግራሞች መካከል የሰው ሃይል አስተዳደር ማሻሻያ ንዑስ ፕሮግራም አንዱ ሲሆን የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት የዚህ ንዑስ ፕሮግራም አንዱ ፕሮጀክት ነው፡፡ ይህንንም መሠረት በማድረግና በአሁኑ ወቅት በሲቪል ሰርቪሱ አሠራር፣ አደረጃጀትና የሰው ሀብት ሥራ አመራር ላይ እየተካሄዱ ያሉ ለውጦችን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የሲቪል ሰርቪስ ሥራዎችን ለመመዘን በሥራ ላይ ያለውን ምዘና ዘዴ ከሥራ ምደባ ወደ ነጥብ የሥራ ምዘና ዘዴ በመቀየር አዲስ የምዘና ሥርዓት ማዕቀፍ ተዘርግቷል፡፡ በመሆኑም የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር 916/2008 በተሰጠው ሥልጠናን ኃላፊነት መሠረት ይህ በአዲሱ የነጥብ የሥራ ምዘና ዘዴ ሥራውን ለማስተግበር ይህን ዝርዝር የመንግሥት ሠራተኞች ድልድል አፈፃፀም መመሪያ አዘጋጅቷል፡፡

ይህ የድልድል አፈጻጸም መመሪያ አራት ክፍሎች አሉት፡፡ የመጀመሪያው ክፍል አጭር ርዕስ፣ የቃላት ትርጉም፣ የመመሪያው ዓላማ፣ መርሆዎች የያዘ ሲሆን፣ ክፍል ሁለት በሠራተኞች ድልድል አፈጻጸም የአዎንታዊ ድጋፍ፣ የደመወዝ ስኬት ሽግግር አፈጻጸም የድልድል ቅድመ ሁኔታ፣ በድልድሉ የልዩ ልዩ አካላት ድርሻ ተዘርዝረዋል፡፡ ክፍል ሶስት የድልድል መስፈረቶችና የነጥብ ድርሻን ያመለክታል፡፡ የመጨረሻው ክፍል አራት ደግሞ በድልድል ወቅት የሚያጋጥሙ ቅሬታዎች አቀራረብና አፈታትን ያመለክታል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የህዝብ አገልግሎት እና የሰው ሀብት ሚኒስቴር

Ministry of Public Service and Human Resources

Similar Directives

ሰኔ 1÷2018
የገቢዎች ሚኒስቴር
Ministry of Revenues
ግንቦት 26፥2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ንብረት አተዳደር ባለስልጣን
Addis Ababa City Public Property Administration Authority
ግንቦት 26፥2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ንብረት አተዳደር ባለስልጣን
Addis Ababa City Public Property Administration Authority