የመመሪያ መለያ: 572/2013
ቀን: ታህሳስ 1፥ 2011 ዓ.ም.
Language: Amharic

የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎችን ለመደገፍ የወጣ የድጋፍ መመሪያ ቁጥር 572/2013

የሳይንስና ቴክኖሎጂ መስፋፋት ለአንድ ሀገር ዕድገት ትልቅ ሚና ያለው ነው፡፡ በዘርፉ እንደ ሀገራት የዕድገት ደረጃና አቅጣጫ የራሱን የተግባራዊነት ምህዳር ይዞ ትልልቅ እንቅስቃሴዎች ይደረጉበታል፡፡ የሀገራትን ዕድገት ዘላቂ ለማድረግ ደግሞ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ልማት አቅም መጠናከር ይኖርበታል፡፡ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ልማት አቅም ከሚተገበርባቸው መንገዶች መካከል አንዱ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚወጡ እውቀቶችንና የፈጠራ ሃሳቦች ወደ ተግባር በመቀየር በኢንድስትሪው ውስጥ እንደ ተግዳሮት/ችግር የተቀመጡ ክፍተቶችን መፍታት ነው፡፡

በሀገራችን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከቴክኖሎጂ ንድፍ አንስቶ እስከ የቴክኖሎጂ ናሙና /ፕሮቶታይፕ/ ድረስ ያሉ የፈጠራ ስራዎች በተሟላ መልኩ ተደግፈው ጥቅም ላይ እንዲውሉ እንደ አንድ ዋና ስራ ይዞ ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ ከዚህ አንፃር ሀገሪቱ እያስመዘገበችው ያለችውን እድገት ተከትሎ ብዙ እውቀቶች እና ቴክኖሎጂዎች ፈልቀው በግብይቱ አለም ውስጥ ጥሰው በመግባት ጠንካራ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲኖራቸው ማስቻል አስፈላጊ ነው፡፡ ስለዚህ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በርካታ ሀገራዊ የቴክኖሎጂ ግብይት ጥናቶች፣ የኮንሴፕት ዴቨሎፕመንት ስራዎች፣ የዲዛይን ተግባራቶች፣የቴክኖሎጂ ናሙና ፕሮቶታይፕ ስራዎች እና የፈጠራ ምርምር ተግባራቶችን በሀገሪቱ ያለውን ሰፊ ክፍተት መሙላት እንዲያስችል፤ በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች ትኩረት ሰጥተው እንዲተገብሩት የማድረግ ሚናን እየተጫወተ ይገኛል፡፡

በሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢኖቬሽን ፖሊሲ ላይ በግልጽ በተቀመጠው መሠረት የሚ/ር መ/ቤቱ ዋነኛ ተግባሩ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ቴክኖሎጂዎችን በፍጥነት የመማር፣ የማላመድ እና የመጠቀም አቅምን መገንባት ነው፡፡ ይህንንም ተግበራዊ ለማድረግ የቅድሚያ ትኩረት በተሰጣቸው ዘርፎች ላይ የተዘጋጁት የቴክኖሎጂ ፍኖተ ካርታዎችን እንደግብዓት አድርጎ ይጠቀምባቸዋል፡፡ በመሆኑም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ተግባራት ጋር በተያያዘ የቴክኖሎጂ ሃሳብ አፍላቂዎችንና ተመራማሪዎችን፣ ውጥና ስርዓት ባለው መንገድ በገንዘብና በቴክኒክ ድጋፍ በመደገፍ የማኅበረሰብን ችግር በቀጥታ ሊፈቱ የሚችሉ የፈጠራ ስራዎች ተግባራዊ እንዲሆኑ ለማስቻል ይህ መመሪያ መቅረፅ አስፈልጓል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር

Ministry of Science and Technology

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration