የመመሪያ መለያ: 855/2014
ቀን: ታኅሣሥ 17፥ 2015 ዓ.ም.
Language: Amharic

የታክስ ውሳኔ ቅሬታ አጣሪ ጽ/ቤት አሠራርን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 855/2014

ታክስ ከፋዮች በያሉበት ት/ጽ/ቤት በታክስ ውሳኔ ላይ ያላቸውን ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉበት ተደራሽነት ያለው፤ በአግባቡ የተደራጀ፤ የተቀላጠፈና ፍትሐዊ የሆነ የውሳኔ ሐሳብ የሚያቅርብ የታክስ ውሳኔ ቅሬታ አጣሪ ጽ/ቤት በማደራጀት የታክስ ከፋዮችን ቅሬታ ለመፍታት የሚያስችል ወጥነት ያለው የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፤

ታክስ ከፋዮች የሚያቀርቡትን የግብር ውሳኔ ቅሬታ በወቅቱና በቅርበት ባለ መረጃና ማስረጃ ለመወሰን፤ ተገቢው ውሳኔ ተወስኖ መከፈል ያለበት ታክስ ቶሎ ወደ ገቢ እንዲቀየር ለማስቻል ፤ ታክስ ከፋዩ የታክስ ውሳኔ ቅሬታውን የሚያቀርበው በሚኒስቴሩ በሚወስንበት የታክስ መጠን በተዋረድ ተከፍሎ በተለየ ሁኔታ ሳይሆን የሚያቀርበውን ቅሬታ መሠረት በማድረግ ታክስ ከፋዩ ባለበት ቅ/ጽ/ቤት ቅሬታውን በማስተናገድ ፍትሐዊነትን ለማስፈንና በታክስ መጠን ያልተገደበ እኩል ተገልጋይነትን ለማረጋገጥ ተገቢ በመሆኑ፤

በታክስ ውሳኔ ላይ ቅሬታዎች የሚታዩበትን የቅሬታ አቀራረብና ምርመራ እንዲሁም የውሳኔ ሐሳብ አቀራረብና የውሳኔ አሰጣጥ ሥርዓት እና የታክስ ውሳኔ ቅሬታ አጣሪ ጽ/ቤት ሥልጣንና ተግባርን ለመወሰን የወጣውን መመሪያ ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

ሚኒስቴሩ በፌደራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (2) መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የገቢዎች ሚኒስቴር

Ministry of Revenues

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration