ወደ አገር ውስጥ በገቡ ዕቃዎች ላይ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ሲፈጸም ከዕቃው የሚፈለግን ቀረጥና ታክሰ መጠን ዋስትና በማስያዝ ዕቃው እንዲለቀቅ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤
የክፍያ ጊዜ ስምምነት በጊዜ የተገደበ፤ ግልፅና ተጠያቂነት ያለበት የተመረጡ አስመጪዎች ፍትሀዊ በሆነ መንገድ የሚስተናገዱበት የአሠራር ሥርዓት እንዲኖረው ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤ ሚኒስቴሩ በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 (እንደተሻሻለ) አንቀጽ 25 ንዑስ አንቀጽ (2) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡