ቴአትር ቤቶች ካላቸው የሥራ ባህሪይ አንፃር እንደ አትራፊ ድርጅቶች የማይታዩ በመሆኑ ለህብረተሰቡ የሚሰጡት አገልግሎት በቀጥታ በገንዘብ ሳይተመን በአስተሳሰብ ላይ ለውጥ እያመጡ ህብረተሰቡን በማዝናናት የሚያስተምሩ ዝግጅቶችን በማቅረብ ጤናማና ምርታማ ዜጋ መፍጠር በመሆኑ አደረጃጀቱና አሰራሩም ይህንኑ ዓላማ የተከተለ ሊሆን ስለሚገባ፣ ኪነ-ጥበብን ለልማት ለማዋል ህብረተሰቡን እያዝናኑ በማስተማር ለሚፈጠረው መልካም አስተዳደር ለሚያበረክቱት የፈጠራ አስተዋጽኦና ለሚሰጡት ድጋፍ በየደረጃው የሚያበረታታና ቴአትር ቤቶችን በገበያ ተወዳዳሪ ለማድረግ ውስጣዊ አሰራሩ ግልጽና ተጠያቂነት ያለበት መሆን ስለሚገባው የውስጥ አሠራር መመሪያ ማውጣት በማስፈለጉ፣
የከተማችን ቴአትር ቤቶች የሚታዩባቸውን የአሠራርና የግብአት ችግሮችን በመቅረፍ የህዝቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ የሚስችል የኪነ-ጥበብ ተቋምና የማስፈጸም አመራር አቅም በመፍጠር ሙያዊ ሚናውን በሚገባ እንዲጫወት ሁኔታዎችን ማመቻቸት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
ቢሮው በተቋቋመበት አዋጅ ቁጥር 35/2004 አንቀጽ 46 ንዑስ አንቀጽ 13 ቢሮው በከተማው አስተዳደር ስር የሚገኙ ቴአትር ቤቶችን እንደሚያስተዳደር፣ እንደሚመራና እንደሚቆጣጠር የተደነገገ ቢሆንም ለቴአትር ቤቶች ተግባርና ኃላፊነታቸውን በግልጽ ያስቀመጠ የውስጥ አሠራር መመሪያ ባለመኖሩ ተግባራት የሚከናወኑት በተለያዩ ኃላፊዎች በሚተላለፉ ደብዳቤዎችና በስብሰባ በሚወሰኑ ቃለ-ጉባኤዎች በመሆኑና ዘመናዊ አደረጃጀት ስላልተፈጠረለት ቢሮው ይህንኑ ችግር ለማስወገድ ነው።