የመመሪያ መለያ: 1033/2017
ቀን: ታኅሣሥ 13፥ 2017 ዓ.ም.
Language: Amharic

የቅባት እህሎች እና የጥራጥሬ ምርቶች የቀጥታ ግብይት መመሪያን ለማሻሻል በተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ላይ የቀረበ አጭር ማብራሪያ (መመሪያ ቁጥር 1033/2017)

ረጅም የግብይት የእሴት ሰንሰለት ለምርት ብክነትና የጥራት መጓደል፤ ህገ ወጥ ግብይት፣ የኮንትሮባንድ መስፋፋት እና ምርትን በክምችት መደበቅ ለመሳሰሉት ችግሮች የሚዳርግ በመሆኑ እና ይህም በውጭ ንግድ አፈጻጸማችን ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ በቅባት እህሎች እና በጥራጥሬ ምርቶች የቀጥታ ግብይት የአሠራር ስርዓት መዘርጋት እንደ አንድ መፍትሄ ተወስዶ የቅባት እህሎች እና የጥራጥሬ ምርቶች የቀጥታ ግብይት መመሪያ ቁጥር 1026/2017 ወጥቶ ተግባራዊ መደረጉ ይታወቃል፡፡

ሆኖም በመመሪያው አንቀጽ 4 ላይ የተካተተው በሰነድ አረጋጋጭ አካል የተረጋገጠና የተመዘገበ ውል የማቅረብ ግዴታ እና ከዚህ ጋር የተያያዙ ሌሎች ግዴታዎች ላኪዎችን እና አቅራቢዎችን ለተጨማሪ ወጪ እና ለተራዘመ የግብይት አፈጻጸም የዳረጋቸው መሆኑን ከወዲሁ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ ወቅቱ የቅባት እህሎች እና የጥራጥሬ ምርቶች ለሀገር ውስጥ እና ለውጪ ገበያ የሚቀርቡበት ወሳኝ ጊዜ በመሆኑ አፋጣኝ ማሻሻያ ካልተደረገ በውጭ ንግድ አፈጻጸማችን እና የውጭ ምንዛሪ ግኝታችን ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል፡፡ በመሆኑም ከውል ጋር የተያያዙ የመመሪያውን ድንጋጌዎች ማሻሻል የቀጥታ ግብብይት ትስስሩን እና የውጭ ንግድ አፈጻጸማችንን የተሳለጠ እንደሚያደርገው ስለታመነበት ይህ የማሻሻያ መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡

መመሪያው በአጠቃላይ 4 አንቀጾችን የያዘ ሲሆን በአንቀጽ 1 አጭር ርዕሱን፣ በአንቀጽ 2 ማሻሻያዎችን፣ በአንቀጽ 3 የመሸጋገሪያድንጋጌን እና በመጨረሻም በአንቀጽ 4 የሚጸናበትን ጊዜ እንዲያካትት ተደርጓል፡፡

የማሻሻያ አንቀጽ 2 በሥራ ላይ ባለው መመሪያ ቁጥር 1026/2017 ላይ ሥልጣን ባለው አካል የተረጋገጠና የተመዘገበ ውል የማቅረብ ግዴታ የሚጥሉትን አንቀጽ 4 ንዑስ አንቀጽ (1) እና 4 (3) እንዲሁም ከዚህ ግዴታ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግንኙነት አላቸው ተብሎ የታመነባቸውን አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ (2) እና 15 (2) በመሰረዝ በአዲስ ድንጋጌ የሚተካ ሲሆን ቀደም ሲል የተደረጉ ውሎችን ተፈጻሚነት በተመለከተም በተዋዋይ ወገኖች ስምምነት እንደሚወሰን የሚገልጽ የመሸጋገሪያ ድንጋጌ አካትቷል፡፡

ስለሆነም የፍትሕ ሚኒስቴር የመመሪያውን አስፈላጊነት ተገንዝቦ እንዲመዘግብልን በአክብሮት አቅርበናል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር

Ministry of Trade and Regional Integration

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration